The Orange Door

Amharic

  

The Orange Door ምንድ ነው?

ይህ በቤተሰብ ሁከት ላጋጠማቸው ሴቶች፤ ህጻናት እና ወጣቶች እንዲሁም ህጻናትና ታዳጊ ወጣት ለሚንከባከቡና ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ቤተሰቦች፤ The Orange Door አዲስ አገልግሎቶች የማቅረቢያ መንገድ ነው።  በ The Orange Door በኩል እርዳታና ድጋፍ ለማግኘት በሌላ አካል መላክ አያስፈልግዎትም።  

The Orange Door ለእኔ ምን ማድረግ ይችላል?

The Orange Door የሚያነጋግሩት
 • የሚቀርብዎት የሆነ ሰው ጉዳት ካደረሰ፤ ከተቆጣጠርዎት ወይም የፍርሃት ስሜት እንዲያድርብዎ ከተደረገ፤ ማለት እንደ የትዳር ጓደኛ፤ የቤተሰብ አባል፤ በቤት አብሮ ነዋሪ ወይም ተንከባካቢ
 • በቤተሰብ ግጭት፤ በገንዘብ ጉዳዮች፤ በህመም፤ በሱሰኝነት፤ በሃዘን ወይም ገለልተኛ በመሆን ምክንያት ከአሳዳጊ መሆን ጋር እየታገሉ ከሆነ 
 • ስለ ህጻን ወይም ታዳጊ ወጣት ደህንነት  የሚያሳስብዎት ከሆነ 
 • ስለ ጓደኛ ወይም የቤተሰብ አባል ደህንነት የሚያሳስብዎት ከሆነ ነው።
እርስዎ ስደተኛ ወይም ጥገኛ ቢሆኑም ወይም ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ባይኖርዎትም፤ ልንረዳዎት እንችላለን። በርስዎ የስደተኛነት ሁኔታ ምክንያት ድጋፍ ከመጠየቅ አይፍሩ።  ይህ በነጻ የሚቀርብ አገልግሎት ነው።የእርስዎን ሁኔታ ጠለቅ ባለ ሁኔታ ለመነጋገር በስልክ ወይም በአካል ቀርበው መወያየት እንደሚፈልጉ ለ The Orange Door ሠራተኞች አሳውቁ።

አስተርጓሚ ያስፈልገኛል

አስተርጓሚ የሚፈልጉ ከሆነ ለአገልግሎቱ ያሳውቁ።  አገልግሎቱ ማወቅ ያለበት:  
 • የእርስዎን ስልክ ቁጥር
 • የርስዎን ቋንቋ
 • ለመደወል ምቹ የሆነ ጊዜ ነው።  
ከዚያ አስተርጓሚ ለእርስዎ መልሶ ይደውላል። .  

The Orange Door አገልግሎት ለእኔ የታቀደ ነውን?

The Orange Door በማንኛውም እድሜ፤ ጾታ፤ ወሲባዊ ፍላጎትና ችሎታ ያሉትን ሰዎች ተቀብሎ ያስተናግዳል። ሁሉም የባህላዊና ሃይማኖታዊ ፍላጎቶች ይከበራሉ። ከወንድ ወይም ሴት ሠራተኛ ጋር መሥራት እንደሚፈልጉ ለሠራተኛው ያሳውቁ።  ለግለሰቦችና ቤተሰቦች የተለያዩ ፍላጎትን ለማሟላት The Orange Door ሠራተኞች ከመድብለ ባህላዊ አገልግሎቶች፤ ከለዝቢያን፣ ከጌይ ሁለት ጺታዊ፤ የተቀየረ ጾታ፤ ውስጣዊ ወሲብ (LGBTI) አገልግሎቶች እና ከአካለ ጕዳተኛ አገልግሎቶች ጋር አብሮ ይሠራል።  ስለሚያስፈልግዎት የአገልግሎቶች ምርጫና መገናኛ መረጃ በሠራተኛ አባል በኩል ይሰጣል።  

The Orange Door የት ነው?

በአካባቢዎ ያሉ የአገልግሎት ዝርዝሮችን ለማየት ወደ www.orangedoor.vic.gov.au ይሂዱ።

The Orange Door የሚከፈተው መቼ ነው?

The Orange Door የሚከፈተው ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጥዋቱ 9am እስከ ከሰዓት በኋላ 5pm ሲሆን (በህዝባዊ በአላት ላይ ይዘጋል)።  

The Orange Door ዝግ በሚሆንበት ጊዜ የት መሄድ አለብኝ?

ከነዚህ ሰዓታት ውጭ የሚከተሉትን አገልግሎቶች ያግኙ:
 • ለወንዶች መጠቆሚያ አገልግሎት (Men’s Referral Service) በስልክ 1300 766 491 (ጥዋቱ ሰዓት 8am እስከ ምሽቱ 9pm ከሰኞ እስከ ዓርብ እንዲሁም ከጥዋቱ ሰዓት 9am እስከ ከሰዓት በኋላ 5pm ቅዳሜና እሁድ) (ለወንዶች የቤተሰብ ሁከት አገልግሎት በስልክ መማክርት፤ መረጃ እና መጠቆሚያ አገልግሎት)
 • ደረጃውን የጠበቀ የቤተሰብ ሁከት ድጋፍ አገልግሎት በስልክ 1800 015 188 (በቀን 24 ሰዓታት፤ በሳምንት 7 ቀናት) ይህም በቤተሰብ ሁከት ሳቢያ ለተበደሉ ሴቶችና ህጻናት ነው።
 • በወንጀል በደል ለደረሰባቸው እርዳታ መስመር (በወንጀል ለተበደሉ እና በቤተሰብ ሁከት ለተበደለ ጐልማሳ ወንድ) በስልክ 1800 819 817 (ከጥዋቱ ሰዓት 8am እስከ ምሽት 11pm በእያንዳንዱ ቀን)
 • በወሲባዊ በደል ችግር ለደረሰበት መስመር፤ ይህ በወሲባዊ በደል ለተጎዱት በስልክ 1800 806 292 (ከሰዓት በኋላ 5pm እስከ ጥዋት 9am ከስኞ እስከ ዓርብ፤ በቀን 24 ሰዓታ ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም ህዝባዊ በአላት)

እርስዎ ወይም ሌላ ሰው አደጋ ውስጥ ከሆኑ ለድንገተኛ ችግር እርዳታ በሶስት ዜሮ (000) ይደውሉ።